ሥነ - ትምህርት
ምዕራፍ 25—ትምህርትና ባሕሪይ
እውነተኛ ትምህርት የሳይንሳዊ ዕውቀትን ፋይዳ ወይም የቀለም ትምህርትን ጠቀሜታ ውድቅ የሚያደርግና የማይቀበል አይደለም፡፡ ነገር ግን ከመረጃዎች በላይ ላለው ኃይል ዋጋ ይሰጣል፡፡ ከኃይልም በላይ ለቸርነት ከሊቃውንት ዕውቀትም በላይ ለባሕሪይ ዋጋ ይሰጣል፡፡ ይህች ዓለም ታላቅ ዕውቀት ካላቸው ሰዎች የበለጠ የተከበረ ባህሪይ ያላቸውን ሰዎች ትፈልጋለች፡፡ ችሎታዎቻቸውን በጽኑ መሠረታዊ ሐሳቦች አማካይነት መቆጣጠር የሚችሉ ሰዎችን ትፈልጋለች፡፡ EDA 250.1
«ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፡፡» «የጠቢባን ምላስ ዕውቀትን ያሳምራል፡፡» ምሣ 4፡7 ምዕ 15፡2 እውነተኛ ትምህርት ይኸን ጥበብ ይሰጣል፡፡ የአንደኛውን ብቻ ሣይሆን የሁሉንም ኃይሎቻችንና እውቀቶቻችን ድንቅ ጥቅም ያስተምረናል፡፡ በመሆኑም ለራሳችን፣ ለዓለምና ለእግዚአብሔር ያለብንን ግዴታ ሁሉ ይሸፍናል፡፡ EDA 250.2
በሰው ልጆች ላይ ከተጣለብን የሥራ ኃላፊነት ሁሉ የባህሪይ ግንባታ እጅግ ዋነኛው ነው፡፡ እጅግ ከፍተኛ ትጋት የሚፈልገው ይህ ጥናትም ባሁኑ ጊዜ የሆነውን ያክል ከዚህ በፊት አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረ የትኛውም ትውልድ እንደዚህ በጣም አስፈላጉ የሆኑ ጉዳዮች ገጥመውት አያውቁም፡፡ ከዚህ ቀደም የነበሩ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች የዛሬዎቹን ወጣቶች እንደገጠማቸው ያለና እፊታቸው የተደቀነ ከባድ አደጋ አልነበረም፡፡ EDA 250.3
ይኸንን ለሚመስል ጊዜ ታዲያ በመስጠት ላይ ያለው የትምህርት መስመር አዝማሚያው ምንድን ነው? ወደ የትኛው ፍላጐት እንድናዘነብል ነው ውትወታው የሚቀርብልን? ራስን ወደ መውደድ፡፡ አብዛኛው የትምህርት ዓይነት የተሳሳተ የስም ለውጥ ብቻ ነው፡፡ በውነተኛ ትምህርት ውስጥ የራስ መውደድ ምኞት ለስልጣን መጓጓት ለሰብዓዊ መብቶችና ፍላጐቶች ንቀት ማሳየት የዓላማችን እርግማን የሆኑ ሁሉ በተቃራኒው አቅጣጫ ይሳባሉ፡፡ እግዚአብሔር ለሕይወት ያወጣው ዕቅድ ለእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር የራሱ ቦታ አለው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱን መክሊቶች እስከ መጨረሻው ደረጃ ማሻሻል አለበት፡፡ ይኸንን በማድረግ ተማኝነት የሚያሳይ የተሰጠው ስጦታ ይነስም ይብዛ ለከፍተኛ ክብር ያበቃዋል፡ በእግዚአብሔረ ዕቅድ ውስጥ ራስ ወዳድነትና ተቀናቃኝ ባለጋራነት ቦታ የለውም፡፡ ራሳቸውን በራሳቸው መዝነው የሚያስቀምጡ ራሳቸውን ከአካባቢአቸው ጋር የሚያነፃጽሩ ሰዎት ጠቢባን አይደሉም፡፡ 2ኛ ቆሮ 10፡12ን ይመልከቱ፡፡ የምናደርገው ነገር ሁሉ «እግዚአብሔር በሚሰጠን ኃይል ነው፡፡» 1ኛ ጴጥ 4፡11 «ለሰው ሣይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት ከጌታ የርስትን ብድራት እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁና የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነውና፡፡» ቆላ 3፡23-24፡፡ እነኝህን መሠረታዊ ሐሳቦች ስንከተል የምንሰጠው አገልግሎትና የምናገኘው ትምህርት ድንቅ ይሆናል፡፡ አሁን በመስጠት ላይ ያለው ትምህርት ግን ከዚህ እጅግ በስፋት ይለያያል፡፡ ሕፃናት ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ እንዲማሩ የሚቀርብላቸው ተማጽኖ መምህሩ የሚለውን ደግመው እንዲሉ ማድረግና በጥላቻ ተቀናቃኝነትን እንዲማሩ ሲሆን የሚሰጣቸው ትምህርት የከፋት ሁሉ ሥር የሆነውን ራስን መውደድን የሚያጐለብት ነው፡፡ EDA 251.1
ስለዚህም የበላይ ለመሆን በመፈለግ ብጥብጥ ይነሳል፡፡ በፈተና ውድድር ብቻ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ስርዓት እየተበረታታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ጤንነትን የሚያጠፋና ለተጠቃሚነትም የማይበጅ ነው፡፡ በብዙ ሌሎች መስመሮችም የባለውን ብቻ መሸምደድ ታማኝ ወደ አለመሆን ይመራል፡፡ በምኞት መቋመጥንና ቅሬታን ለማስፋፋት ሕይወትን መራራ የሚያደርጋት ሲሆን ዓለምንም በእነኛ ለሕብረሰብ አስጊ አደጋ የሚሆኑ ረፍት የሌላቸውና ከቁጥጥር ውጪ የሚያደርጉ መንፈሶችን ይረዳል፡፡ EDA 252.1
አደጋው በዘዴዎቹ ውስጥ የሚገባ ብቻ ሳይሆን በሚጠናው ትምህርት ውስጥም ነው፡፡ EDA 252.2
እድሜ ልክ አጣራጣሪ የሆኑ የሕይወት ዘመናት ውስጥ የወጣቱ አዕምሮ ሄዶ ሄዶ የሚያርፍባቸው ሥራዎች ምንድን ናቸው? ቋንቋንና ሥነ ጽሑፍን በተመለከተ ወጣቱ መጠጣት ያለበት ከየትኛው ፏፏቴ ነው? ከሃይማኖት የለሾች ጉድጓድ ነው ወይስ በተለያዩ ቅሌቶች ከተበከለው የጥንት ባዕድ አምልኮ ምንጮች ተቀድቶ ከሚሰጠው ከእነዚህ ምንጮች ነው? ለጥናት ደራሲያን ድብቅ ናቸው፡፡ ለሥነ ምግባር መሠረታዊ ሐሳቦች ከበሬታ የማይሰጡ መሆናቸው ክርክር የለውም፡፡ ይኸንን አባባል ለስንቱ ዘመናዊ ደራሲያን ደጋግመን ማለት እንችላለን በቋንቋ ፀጋና ውበት ኖሮአቸው ሳለ መሠረታዊ ሐሳቦችን በመናቅ በራሳቸው ቅርፀቢስነት ምክንያት ከንባቢው ጋር የሚጣሉና የሚለያዩ ስንት ናቸው፡፡ EDA 252.3
ከነዚህም በተጨማሪ በቀላሉ እያዝናኑ ወደሚያስደስት ያሸበረቀ ሕልም የሚያመሩ ልበ ወለድ ደራሲያን ተበራክተዋል፡፡ እነኚህ ደራሲያን በፀረ ግብረገብ በግባር ለመከሰስ ይፋ አልወጡ ይሆናል፡፡ ሥራቸው ግን እጅግ አስጊና አደገኛ ሁኔታ የተቀላቀለበት ነው፡፡ የሕይወትን ጥብቅ ችግሮች የሚፈልጉትን ሺህ በሺህ የሚቆጠር ጊዜ ጉልበትና የግል ሥነ ምግባርን የሚቀማ ነው፡፡ EDA 252.4
በሳይንስ ጥናት ውስጥ አጠቃላይ ክትትሉና ዓላማው ያንኑ ያክል ትልቅ አደጋ አለበት፡፡ አዝጋሚ ለውጥ የተባለው ጥናትና ከርሱ ጋር ዝምድና ያላቸው ስህተቶች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ከአፀደ ሕፃናት እስከ ኮሌጅ ድረስ በትምህርትነት ይሰጣሉ፡፡ ስለሆነም የሳይንስ ጥናት የእግዚአብሐርን እውቀት በማካፈል ፈንታ ታማኝ ወደ አለመሆን የሚያዘነብል ከሰዎች ግምታዊ ሐሳቦችና ንድፈ ሐሳቦች ጋር ተቀላቅሏል፡፡ EDA 253.1
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ቢሆን ዘወትር በትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥናቱ የሚሰጥበት አኳኂን ከእግዚአብሐር ቃል ያለክፍያ የሚገኙ መዝገባችን በሚቀማ መልኩ ነው፡፡ «ከፍተኛ ትችት» የተባለው አሠራር ግምት ላይ የተመሠረተ ሐሳብ በየከፍሎቹ ወይም ምዕራፎቹ ላይ በሚደረግ ግምገማ ላይ የመጣለትን መናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንደ የመለኮት መግለጫ የመሆኑን እምነት የሚያጠፉ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ያለውን የመቆጣጠር የማነሳሳትና የሰዎችን ሕይወት በመንፈስ የመሙላትን ኃይል የሚነጥቅ ነው፡፡ EDA 253.2
ወጣቶች ወደ ዓለም ሲወጡ ወደ ኃጢአት የሚስቡ የሚማርኩ አስተያየቶችን ገንዘብ የመፈለግ ጉጉት ለደሰታና ወደ ብልግና ለእይታ ለምቾት እና አባካኝነት ቅጡ የጠፋበት ምኞተኛ መሆን አጭበርባሪነትና ቀማኛነትና ውድመት ሲጋረጥባቸው ይኸንን ለመጋፈጥ ለዚህ የሚሆኑ ትምህርቶች ታዲያ ምንድን ናቸው? EDA 253.3
መንፈሳዊነት ሰዎች ፍፁም መለኮታዊ ሆነው ሳለ በከፊል ሰብዓዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ «እውነተኛ እውቀት ሰዎችን ከህግ በላይ» እንደሚያስቀምጣቸው «የተሠሩ ኃጢአቶች ሁሉ በየዋህነት እንደተፈጸሙ» «የሆነው ነገር ሁሉ ትክክል እንደሆነ» እና «እግዚአብሔርም የሚያወግዝ እንዳልሆነ» ያረጋግጣል፡፡ የሰው ልጆች መኖሪያ ሠፈር በሰማይ እንደሚወከለው እዚያም እጅግ በከፍተኛ ደረጃ የተከበረ ነው፡፡ ስለዚህም ለሰዎች እንዲህ ይላል «ማንኛውንም ነገር ሁሉ ብትሠራ ምንም አይደለም፡፡ ደስ እንደሚያሰኝህ ሆነህ ኑሮ ሰማይ ቤትህ ነው፡፡»ስለዚህም በርካታ ሕዝብ ፍላጐት ማለት ከፍተኛው ሕግ ነው ወደሚለው ሐሳብ በማዘንበል ወደ ማመን ያመራሉ፡፡ ነፃነት ማለት ሕጋዊ ፈቃድ እንደሆነና ሰውም ተጠያቂነቱ ለራሱ ብቻ እንደሆነ ወደማመን ይዞራሉ፡፡ EDA 253.4
ገና በሕይወት መጀመሪያ ላይ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ሲሰጥ ወደኋላ ግፊቱ እየበረታ ሲሄድ የራስ ጥንካሬና ንጽህና እጅግ የሚያስፈልግበት ሰዓት ሲመጣ እነኝህ ልዩ ችሎታዎች መከላከያ ከየት ይገኛሉ? ዓለምንስ ሁለተኛዋ ሶዶም ከመሆን የሚያድናት ምንድን ነው? EDA 254.1
በዚሁ ላይ ደግሞ ሥርዓት አልበኝነት መለኮታዊውን ብቻ ሣይሆን ሰብዓዊዮን ሕግም ጭምር ጠራርጐ ማጥፋት ይፈልጋል፡፡ ሀብትና ሥልጣንን የማሰባሰብ በብዙኃኑ ወጪ ጥቂቶችን ማበልፀግ ድኃውን መደብ ከፍላጐታቸው ከጥያቄአቸው አንፃር አሰባስበው እንደመከላከያ መጠቀሚያ ከማድረግ የእረፍት የለሽነት መንፈስ የብጥብጥ የም መፋሰስ የፈረንሣይ አብዮት ያመጣቸውን ሃሣቦች የያዙ ትምህርቶች ዓለም አቀፍአዊ ሥርጭት ሁሉ መላዋ ዓለም ፈረንሳይን ወደአወካት ብጥብጥ ዓይነት ትግል ውስጥ እንድትገባ የሚገፋፋ ነው፡፡ EDA 254.2
ለዛሬ ወጣቶች እፊታቸው የተደቀነው ስበት ይኸን የሚመስል ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ከባድና ድንገተኛ ለውጥ መካከል ፀንተው ለመቆም አሁን የባህሪ መሠረት መጣል አለባቸው፡፡ EDA 254.3
በየትውልዱና በየሃገሩ የባሕርይ ግንባታ እውነተኛ መሠረትና አሠራሩ ያው አንድ ነው፡፡ የመለኮት ሕግ «ጌታ አምላክህን በፍፁም ልብህ ውደድ... ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡» ሉቃ 10፡27 በመድህናችን ባሕሪና ሕይወት ውስጥ የተገለጡት መሠረታዊ ሐሳቦች አስተማማኝ ብቸኛ መሠረትና ብቸኛው እርግጠኛ መመሪያም ነው፡፡ EDA 255.1
«የጊዜው መረጋጋትና የደስታህ ብርታት ጥበብን እውቀት ይሆናል» ኢሳ 33፡16 /እንደ ሊሰር አተረጓጐም/ ከእግዚአብሔር ቃል ብቻ ተከፍሎ ሊሰጥ የሚችል እውቀትና ጥበብ ነው፡፡ EDA 255.2
የርሱን ትዕዛዞች እሰራኤሎች እንዲጠብቋቸው በታዘዙ ጊዜ እነኛ ቃላት እውነት የነበሩትን ያክል አሁንም እውነት ናቸው፡፡ «በአህዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፡፡» ዘዳ 4፡6 EDA 255.3
ለግለሰቡ መረጋጋት ለቤት ውስጥ ንጽህና ለሕብረተሰቡ ደህንነትና ለሀገሩ ሕዝብ መረጋጋት ብቸኛው ዋስትና እዚህ ላይ ብቻ ነው፡፡ ከሕይወት ውስብስብ ችግሮች አደጋዎችና አዋጊ በሆኑ የይግባኛል ጥያቄዎች መካከል መፈጸም ያለበት ደህናውና እርግጠኛው መንገድ እግዚአብሔር የሚለውን መፈጸም ብቻ ነው፡፡ «የእግዚአብሐር ሥርዓት ቅን ነው፡፡» «እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም፡፡» መዝ 19፡8፡15፡5 EDA 255.4