የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
ምዕራፍ ፯—የቤተ ክርስቲያኒቱ እትሞች፡፡
የማተሚያ ቤት ሥራችን በእግዚአብሔር መሪነት በተለይም በአርቆ ተመልካችነቱ የተቋቂመ ነው፡፡ የተለየ ሐሳብ ለመፈጸም የታሰበ ነው፡፡ ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶች የተለየ ሕዝብ ከዓለም የተለዩ ሆነው በእግዚአብሔር ተመርጠዋል፡፡ በታላቁ የእምነት መቁረጫ እርሱ ከዓለም የደንጊያ ቦታ ቆርጦአቸው፤ ከራሱ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ አምጥቶአቸዋል፡፡ እንደራሴዎቹ አድርጎዋቸል፤ በጨረሻው የደህንነት ሥራ ለርሱ መልእክተኞች (አባሳደርስ) እንዲሆኑ ጠርቶአቸዋል፡፡ ለሟቾች ካሁን ቀደም ከተላከው እጅግ የጠበቁና (የተከበሩና) አስፈሪ የሆኑትን ማስጠንቀቂያዎች ለዓለም ይሰጡ ዘንድ ለነሱ አደራ ተሰጥተዋል፤ ይህንንም ሥራ በፈጸም ላይ የማተሚያ ቤቶቻችን እጅግ ጠቃሚዎች ከሆኑት አማካዮች መኻከል ናቸው፡፡ CCh 70.1
ከማተሚያ ቤቶቻችን ታትመው የሚወጡ ጽሑፎች እግዚአብሔር ይገናኙ ዘንድ ሕዝብን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ፩1 CCh 70.2
ከሌላው ይልቅ በጣም ዋና /ጠቃሚ/ የሆነ አንድ ሥራ ካለ፤ በሕዝብ ፊት ጽሑፎቻችን እንዲደርሱ ማድረግ ነው፤ እንዲሁም ቅዱሣት መጽሕፍትን እንዲመረምሩ እነሱን መምራት ነው፡፡ ወንጌላዊ ሥራ ማለት ጽሑፎቻችንን ለቤተሰቦች ማድረስ (ማስተዋወቅ) ከነሱ ጋር መነጋገርና መጸለይ ለነሱም መጸለይ መልካም ሥራ ነው፤ የቅስናም (የፓስተር) ተግባር ያደርጉ ዘንድ ወንዶችንም፤ ሴቶችንም የሚያሠለጥን ነገር ነው፡፡ ፪2 CCh 70.3
ጽሑፎቻችንን መሸጥ ዋናና ለወንጌላዊ ሥራ እጅግ ጠቃሚ የሆነ መሥመር ነው፡፡ ጽሑፎቻችን የወንጌል ስብሰባ ሊደረግ ወደማይቻልበት ሥፍራዎች ሊሔዱ ይችላሉ፡፡ በእንዲህ ያሉ ሥፍራዎች ታማኙ ወንጌላዊ መጽሐፍ ሻጭ የንቁ ሰሰኪ ስፍራ ይወስዳል፡፡ መጽሐፍን በመሸጥ በማደረገው ሥራ ያለዚህ ከቶ ሊሰሙት ለማይቻላቸው ለብዙ ሺህ ሰዎች እውነቱ ይቀርባል፡፡ CCh 70.4
መጽሐፍ ሻጮች፤ ወዳገሩ ልዩ ልዩ ክፍሎች መሔድ አለባቸው ይህ ሥራ ጠቃሚነቱ ከስብከተ አገልግሎት ጋር እኩል ነው፡፡ ንቁ የሆነ ሰባኪና የረጋ መልእክተኛ በፊታችን ያለውን ታላቅ ሥራ ለመፈጸም ሁለቱም ያስፈልጋል፡፡ ፫3 CCh 70.5
በመጽሐፎቻችን ውስጥ ያለውን ብርሃን በሕዝብ ፊት እንድናቀርብ እግዚአብሔር የመጽሐፍን መሸጥ ሥራ መሣርያ አድርጎት አዝዋል ስለዚህ መጽሐፍ ሻጮች ለመንፈሳዊ ዕውቀታቸውና ማብራሪያቸው የሚያስፈጉትን መጻሕፍት በዓለም ፊት በተቻለው ፍጥነት ማቅረብ ጠቃሚነት ያለው መሆኑ ሊታወሳቸው ይገባል፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታ ሕዝቡ እንዲያደርግ የሚፈልገበት ይህንኑ ሥራ ነው፡፡ በመጽሐፍ ሻጩ በማደረገው ጥረት አማካይነት ባይሆን ኑሮ፤ ብዙዎች ማሰጠንቀቂያውን ከቶ ባልሰሙ ነበር፡፡ ፬4 CCh 70.6
ጽሑፎቻችን ወደ የሥፍራው መነዛት አለባቸው፡፡ በብዙ ቋንቋዎች ታትመው ይውጡ፡፡ የሶስተኛው መልአክ መልእክት በዚሁ አማካይነትና ንቁ በሆነው አስተማሪ አማካይነት መሰጠት አለበት፡፡ አንተ ለዚህ ጊዜ የሚሆነውን እውነት የምታምን ንቃ፡፡ ያውጁት ዘንድ እውነትን የሚያስተውሉትን ለመርዳት የሚቻልበትን ገንዘብ (መርጃ) ሁሉ ማምጣት አሁን ተግባርህ ነው ከጽሑፎቻችን ሽያጭ የሚገባ ገሚሱ ገንዘብ የታወሩትን ዓይኖች የሚከፍትና የልብን ፈር የሚያርሰውን ተጨማሪ ጽሑፍ ለማበርከት አቅማችንን ይጨምርልን ዘንድ ልንጠቀምበት አለብን ፭፡፡5 CCh 71.1
ሰዎች ትጉ ከሆነው ሰባኪ መልእክቱን ከሚሰሙበት ሥፍራ እንኳ መጽሐፍ ሻጩ ከሰባኪው ጋር በመተባበር ሥራውን ማካሔድ እንዳለበት ተነገረኝ፡፡ ሰባኪው በተማኝነት መልእክቱን ቢያቀርብላቸውም እንኳ ሰዎቹ ሁሉን ማስታወስ አይችሉምና፡፡ ስለዚህ የታተመው ገጽ አስፈላጊ ነው ለዚህም ጊዜ ወደሚሆነው ጠቃሚ እውኑት የሚያነቃቃቸው ብቻ ሳይሆን ግን በእውነት እያጸናቸውና እየመሠረታቸው ከሚያስተው ስህተት እንዲጠበቁ ያደርጋቸዋል፡፡ የታተሙት ጽሑፎችና መጽሐፍት ለዚህ ጊዜ የሚሆነውን መልእክት በሕዝብ ፊት ዘወትር ለመጠበቅ የጌታ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ለነፍሳት እውነት እንደብራራላቸውና እንዲጸኑበት ለማድረግ በቃለ ስብከት ብቻ ሊፈጸም ከሚቻለው ይልቅ ጽሑፎቹ እጅግ ታላቅ የሆነ ይራ የሚሠሩ ናቸው፡፡ የረጉ መልእክተኞች በጽሐፍ ሻጩ ሥራ አማካይነት በሰዎች ቤት የተቀመጡ በማናቸውም መንገድ ሁሉ የወንጌልን አገልግሎት ያጠነክራሉ፤ የቃልን ስብከት የሚሰሙትን መንፈስ ቅዱስ ለልባቸው እንደሚያሳትፋቸው እንደዚሁም መጽሐፎቹን ሲያነቡ ሳለ ለሐሳባቸው ያሳትፍላቸዋልና፡፡ የመላእክት አገልግሎት የሰባኪውን ሥራ እነደሚደግፍ እንደዚሁም ያው እውነት ያለባቸውን መጽሐፎች የማደግፍ ነው፡፡ ፯6 CCh 71.2
ከፈለጉ፤ እነዚህን መጽሐፎች በመሸጥ ለትምህርት ቤት የሚከፈለውን እንደያተርፉ የተገቡተን ተማሮች ለመርዳት በብልሃት እቅዶች /ፐላን/ ይታቀዱላቸው በያዙት ኮርስ ለማዝለቅ ከማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶቻችን ለአንደኛው ለመክፈል በዚህ ጐዳና በቂ ገንዘብ የሚያተርፉ በሌሎች ጣቢያዎች ተቀዳሚነት ያለውን ወንጌላዊ ሥራ ይሠሩ ዘንድ ተገቢዎች ሊያደርጋቸው የሚረዳቸውን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ዓይነተኛ ልምምድ ያገኛሉ፡፡፮7 CCh 71.3
የቤተ ክርስቲያን አባሎቻችን ጽሑፎቻችንን ማደል ጠቃሚ መሆኑን ስገነዘቡ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ለዚህ ሥራ ቀድሰው ይሰጣሉ፡፡ ፰8 CCh 71.4
የምሕረት ጊዜ እንደቀጠለ መጠን ለመጽሐፍ ሻጩ ምቹ ጊዜ ይኖረዋል፡፡፱9 CCh 71.5
ወንድሞቼና እህቶቼ ጽሑፎችን የሚያትም ድርጅትን በጸሎታችሁና በገንዘባችሁ ትደገፈ ዘንድ ከልባችሁ ብትታጠቁበት ጌታ ደስ ይለዋል፡፡ የእግዚአብሔር የብልጽግናውን በረከት እንዲቀበል በየጧትና በየማታው ጸልዩ መነቃቀፍንና መወቃቀስን አትድፈሩ፡፡ ከከንፈሮቻችሁ ማጉረምረምና ወቀሳ አይውጣ፤ መላእክት እነዚህን ቃላት የሚሰሙ መሆናቸውን አስቡ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የእግዚአብሔር አቋም መሆናቸውን እንዲያዩ ሁሉም መመራት አለባቸው፡፡ ለገዛ ራሳቸው ጥቅም ያከባክቡ (ያገለግሉ) ዘንድ፤ ከቁም ነገር የማይቆጥሩዋቸው ላምላክ ሃሳብ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እርሱ ከሥራው ጋር የተያያዘውን ነገር ሁሉ የተቀደሰ አድርገው እንዲይዙት ያስባል፡፡ ፲10 CCh 71.6