የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

18/126

ምዕራፍ ፭—የፀሐይ ግባት ጸሎት

ብዙዎች ሰንበት ጠባቂዎች ነን የሚሉ በቅድስና ከሚጠብቁት ይልቅ እጅግ የበለጠ ቅድስና ከሰንበት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጌታ ሰንበትን በትእዛዙ መሠት በቃለም ሆነ በመንፈስ ባለጠበቁት እጅግ ተወርዶዋል፡፡ ሰንበትን በመጠበቅ ረገድ እንዲታደሱ (ሪፎርም) ይፈልግባቸዋል፡፡ CCh 46.1

ከፀሐይ ግባት በፊት የቤተሰብ አባሎች የእግዚአብሔርንቃል ለማንበብ ለመዘመርና ለመጸለይ ይሰብሰቡ፡፡ ብዙዎቹ ቸልተኞች ስለሆኑ እዚህ ላይ መቃናት (ሪፎርም) ያስፈልጋለ፡፡ ለእግዚአብሔርና ለእርስ በርሳችን መናዘዝ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር የባረከውንና የቀደሰውን ቀን ያከብር ዘንድ የቤተሰብ አባል ሁሉ እንዲዘጋጅ የተለዩ ውሳኔዎች ለማድረግ እንደገና መጀመር አለብን፡፡ CCh 46.2

በቤተሰብ ጸሎት ልጆች ተካፋዮች ይሁኑ፡፡ ሁላቸው መጽሐፍ ቅዱሶቻቸውን ያምጡና እያንዳንዳቸው አንድ ቁጥር ወይም ሁለት ያንብቡ፡፡ ከዚያ በኋላ ዕውቅ የሆነ መዝሙር ጸሎት የሚከተለው ይዘመር፡፡ ስለዚሁ ክርስቶስ ምሳሌ ሰጥቶናል፡፡ የጌታ ጸሎት በዘልማድ እንዲደገም የታሰበ አይደለም፤ ግን ጸሎታችን ግልጽ ከልብ የሆነና የተስተዋለ እንዲሆን የሚገለጽ መግለጫ ነው፡፡ በተስተዋለው ልመና ለጌታ ፍላጎቶችህን ንገረውና ስለ ምሕረቱም ምሥጋና አቅርብለት፡፡ በእንዲህ የሱስን ወደ ቤትህና ወደ ልብህ የምትቀበለው እንግዳ አድርገህ ታድመዋለህ፡፡ ስለ ሩቅ ነገሮች በቤተሰብ ረጅም ጸሎት ማድረግ በሥፍራውም የለም፡፡ የጸሎት ሰዓት እንደ ዕድልና በረከት ሊቆጠር የሚገባ ሲሆን የሚያሰለች ያደርገዋል፡፡ ጊዜውን የመደሰቻና የፍስሐ ጊዜ አድረገው፡፡ CCh 46.3

ፀሐይ ስትባ (ሰንበት ሲያበቃ) የጸሎት ድምፅና የምሥጋና መዝሙር የተቀደሱት ሰዓታት የሚዘጉበትን (የሚያበቁበትን) ጊዜ ያመለክትና በሚጀመረውም በሳምንቱ የትዳር ሐሳብ እግዚአብሔር እንዲገኝበት ያድመው፡፡ CCh 46.4

ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን አድርጎ ሰንበትን መጠበቅ ዘለዓለማዊ ደህንነት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር «ያከበረኝን አከብራለሁና” ይላል፡፡ ሳሙኤል ቀዳማዊ ፪፡፴፡፡ CCh 46.5