የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
ማሳሰቢያ፡
ምዕራፍ ፩—ክርስቶስን ለመገናኘት መዘጋጀት ፡፡
ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶች የሱስ ያዘጋጅላቸው ዘንድ ወደ ሔደበት የተዋበ መኖሪያ ሊወስዳቸው የሚመጣበትን ጊዜ በናፍቆት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ በዚያ ሰማያዊ መኖሪያ ኃጢአት፣ ሐዘን፣ ረሐብ፣ ድኅነት፣ በሽታና ሞት የሉም፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ ለታመኑት የሚቆያቸውን እድል ባሰበ ጊዜ፤ ‹‹እዩ እንዴት ያለውን ፍቅር ሰጠነ አብ የእግዚአብሔር ልጆች እንባል ዘንድ፣ አሁነ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡፡ ገናም ምን እንደምንሆን አልተገለጠም ነገር ግን እርሱ በተገለጠ ጊዜ እንደርሱ እንድንሆን አወቅነ›› ከማለት በቀር ምንም ለማለት አልቻለም፡፡ ( ዮሐንስ መል (፣(፣( ፡፡ CCh 1.1
የእግዚአብሔር ዓላማ የሕዝቡ ጠባይ እንደ ክርስቶስ ጠባይ እንዲሆን ነው፡፡ ሲጀመር ጀምሮ በአምሳሉ የተፈጠሩት የሰብዓዊ ቤተሰብ አባሎች የእግዚአብሔርን ጠባይ የሚመስል እንዲያገኙ ያምላክ እቅድ ነበር፡፡ ይህንን ለመፈጸም የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ከክርስቶስና ከመላእክት ጋር ፊት ለፊት በመነጋገር ምክሮችን መቀበል ነበረባቸው፡፡ ግን ከበደሉ በኋላ በዚህ አኳኋን ከሰማያዊ ፍጥረቶች ጋር በነጻ መነጋገር አልተቻላቸውም፡፡ CCh 1.2
ሰው ያለ መሪ እንዳይቀር እግዚአብሔር ለሕዝቡ ፈቃዱን ሊገልጽ ሌሎችን ዘዴዎች መረጠ፤ ከነዚህም ከፍ ያለው ዘዴ በነቢያት አማካይነት መነጋገር ነው፤ እነዚህም የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ ሊያደርሱ የተፈለጉት ነቢያት ወንዶችም ሴቶችም ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ‹‹በመኻከላችሁ ነቢይ ሰው ቢኖር እኔ እግዚበእሔር በራዕይ እገለጥለታለሁ ወይም በሕልም እናገርዋለሁ›› ብሎ ተናግሮአል፡፡ ዘሁልቁ (( ፣ (፡፡ CCh 1.3
እግዚአብሔር ያሰበው ሕዝቡ ስለሚኖርበት ጊዜ እንዲያውቅ ብቻ ሳይሆን ስለሚመጣውም ጊዜ እንዲያስተውል ጭምር ነው፡፡ እግዚአብሔር ነገር አያደርግምና ምሥጢሩን ለባሮቹ ለነቢያት ካልነገረ›› (አሞጽ፣(፣()፡፡ ይህም፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ‹‹የብርሃን ልጆች›› (( ተሰሎንቄ (፣() ከዓለም ሕዝብ ልዩ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ CCh 1.4
የነቢይ ሥራ ትንቢት መናገር ብቻ አይደለም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስድስቱን መጻሕፍት የጻፈው ለወደፊት ስለሚሆነው ነገር ብዙ ትንቢት አልተናገረም፡፡ ሥራውን ሆሴዕ ሰፋ ባለ ሐሳብ አብራርቶታል፡፡ ‹‹ነገር ግን በነቢይ እጅ እግዚአብሔር እሥራኤልን ከምሥር አወጣ በነቢዩም እጅ ጠበቀው››፡፡ (ሆሴዕ ((፣() ፡፡ CCh 1.5
ነቢይን የሰውን ልብ ሊያይና ሊያውቅ የሚችል እግዚአብሔር የመረጠ ነው እንጂ ሰው የመረጠው ወይም በራሱ የተመረጠ አይደለም፡፡ ወንዶችንም ሴቶችንም ለርሱ እዲናገሩ እግዚአብሔር በየጊዜው እንደመረጣቸው በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ግልጽ ሆኖ ይገኛል፡፡ CCh 1.6
እነዚህ መገናኛ እንዲሆኑ እግዚአብሔር የመረጣቸው ነቢያት በቅዱስ ራእይ የገለፀላቸውን ተናግረዋል፤ ጽፈዋልም፡፡ መልእክታቸው ተከበረው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ በነዚህ ነቢያት አማካይነት የሰብዓዊ ቤተሰብ አባሎች ለሰዎች ነፍሳት የሚደረገውን ተጋድሎ፤ ክርስቶስም ከመላእክቱ ጋር ሁኖ በሰ ይጣንና በመላእክቱ ላይ የሚያደርገውን ውጊያ እንዲያስተውሉ ተመርተዋል፡፡ ስለዚሁ ተጋድሎና፤ እግዚአብሔር ለሥራው በመጠንቀቅ ስላበጀው ዘዴና ጌታቸውን ለመገናኘት የሚጠባበቁትን የወንዶችንም የሴቶችንም ጠባይ ፍጹም ለማድረግ ያበጀውን ብልሃትም በመጨረሻዎቹ ቀኖች እንድናስተውል ተመርተናል፡፡ CCh 1.7
ሐዋርያት የመጨረሻዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፎች ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት ሁኔታዎች ግልጽ የሆነ ሐሳብ ሰጥተውናል፡፡ ጳውሎስ ስለ ‹‹ክፉ ጊዜ›› ጻፈ፤ ጴጥሮስም፤ ‹‹ወዴት አለ የመምጣቱ ተስፋ›› እያሉ ስለሚጠይቁ በገዛ ፍትወታቸው ስለሚሔዱ ፌዘኞች አስጠንቅቆናል››፡፡ በዚህ ጊዜ ያለችው ቤተክርስቲያን በተጋድሎ ላይ ልትሆን ነው፤ ዮሐንስ ሰይጣንን ‹‹ከቀሩት ዘርዋ ጋራ ሰልፍ ሊያደርግ ሲወጣ›› አይቶታልና፡፡ CCh 2.1
የሱስ ከምጣቱ በፊት እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፎች እግዚአብሔር ለሕዝቡ የተለየ ብርሃንና እርዳታ ለመስጠት ማቀዱን ተመለከቱ፡፡ CCh 2.2
የክርስቶስን ዳገመኛ መምጣት ተስፋ አድርጋ የምትጠባበቀው ቤተክርስቲያን (የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን) ምንም ዓይነት ሥጦታ ያልጎደላት (፩ ቆሮ ፩፣ ፯፣ ፰) መሆንዋን ጳውሎስ ይናገራል፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን የተባበረች፤ የደረጀች፤ በመልካም መሪዎችዋ የተባረከችና የትንቢት መንፈስ ሥጦታ ያላት ናት፤ በውስጧም ሐዋርያት፤ ነቢያት፤ ወንጌላውያን፤ ቄሶችና (ፓስተር) አስተማሮች ይገኛሉ፡፡ (ኤፌ ፬፤ ፲፩)፡፡ CCh 2.3
የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ‹‹የቅሬታዋን ቤተክርስቲያን›› አባሎች ሐዋርያው ዮሐንስ ‹‹የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ›› (ራእይ ፲፪፣ ፲፯) ይላቸዋል፡፡ ስለዚህ ትእዛዝ አክባሪ ቤተክርስቲያን ናት ማለት ነው፡፡ ይህችም የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ‹‹የየሱስ ምስክር›› የሆነው፤ ‹‹የትንቢት መንፈስ›› ያላት ናት፡፡ (ራእይ ፲፱፤ ፲)፡፡ CCh 2.4
እንግዲህ በእግዚአብሔር እቅድ ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን (ባለ ትንቢትዋ ቤተክርስቲያን) በተነሳች ጊዜ በውስጧ የትንቢት መንፈስ ያላት መሆንዋ ግልጽ ነው፡፡ ባለፉት ክፍለ ዘመናት ሕዝቡ የተለየ ፍላጎት በነበረው ጊዜያት እግዚአብሔር እንደተናገረው ትግሉ በሚብስበትና ዘመኖቹም የከፉ በሚሆኑበት ጊዜ (በመጨረሻዎቹ ቀናት) ለሕዝቡ መናገሩ ተገቢ ነው፡፡ CCh 2.5
ይህች ባለ ትንቢትዋ ቤተክርስቲያን (ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት) ልክ በትንቢቱ በተወሳው ዘመን በተነሣች ጊዜ ከአንድ መቶ ጥቂት በለጥ ካለ ዓመት በፊት፤ ‹‹እግዚአብሔር በተቀደሰው ራእይ አሳይቶኛል›› የሚል ድምፅ በመኻከላችን ተሰማ፡፡ CCh 2.6
ይህ የትዕቢት አነጋገር ሳይሆን ለእግዚአብሔር እንድትናገር የተጠራች የአሥራ ሰባት ዓመት ልጅ የተናገረችው ቃል ነው፡፡ ሰብዓ ዓመት ሙሉ ባደረገችው አገልግሎት ያ ድምጽ በመኻከላችን ሲመራን፤ ሲያርመን፤ ሲያስተምረን ኖረ፡፡ ያ ድምጽ ዛሬም እግዚአብሔር በመረጣት መልእክተኛው በሚስስ ኢ ጂ ኋይት ከተጻፉት ብዙ ሺህ ገጾች ሲሰማ ይኖራል፡፡ CCh 2.7