የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
«አዎን” አልሁ፡፡
«እንግዲያውስ እንደ ተረሳሽና ተስፋ ቢስ መሆንሽ ለምን ይሰማሻል? ይህ የጠላት ሥራ አይደለምን? አልሁም፤ «እንዲሁ መሆኑን አምናለሁ!»፡፡ CCh 19.4
«እንባዬን በተቻለኝ ፍጥነት ጠራረግሁና ፤ «እንግዲህ ይበቃል፤ ከእንግዲህ በጨለማ በኩል አልመለከትም፡፡ ብኖርም፤ ብሞትም ነፍሴን ይጠብቅልኝ ዘንድ ለሞተልኝ አደራ እሰጠዋለሁ፡፡ CCh 19.5
«ከዚያ በኋላ፤ እግዚአብሔር ሁሉን ነገሮች ደህና እንደሚያደርግልኝ አመንሁ፤ በዚህ ረዳተቢስ በሆንሁበት ስምንት ወራት ውስጥ ምንም ተስፋ መቁረጥ ወይም ጥርጣሬ አልነበረብኝም፡፡ አሁን ይህን ነገር፤ የጌታ ታላቁ ፕላን (እቅድ) መሆኑን፤ እዚህ አገር ለሕዝቡ ጥቅም፤ ለነዚያም በአሜሪካ ላሉትና ለጥቅሜ መሆኑን እመለከታለሁ፡፡ ለምን ወይም ስለምን እንደሆነ ልገልጽ አልችልም፤ ግን አምነዋለሁ፡፡ በመከራዬም ደስ ይለኛል፡፡ ሰማያዊ አባቴን ልታመነው እችላለሁ፡፡ ፍቅሩን አልጠራጠርም፡፡ CCh 19.6
ሚስስ ኋይት፤ በቤትዋ በካልፎርኒያ ስትኖር በመጨረሻው አሥራ አምስቱ የሕይወቷ ዓመታት ውስጥ እየሸመገለች ሔደች፤ ነገር ግን በትንሹ የእርሻ ሥራ፤ በሥራዋም ለረዱት ለቤተሰቦቻቸው በጎ አድራጎት በመሥራት ተደሰተች፡፡ በጽሕፈት ተግታ ስትሠራ እናገኛታለን፤ ብዙ ጊዜም ቀደም ብላ ተኝታ፤ ከእኩለ ሌሊትም በኋላ ሥራዋን ትጀምር ነበር፡፡ አስደሳች ቀን የሆነ እንደሆነ ሥራዋ ከፈቀደላት ወደ ገጠር ትሔድ ነበር፤ በአትክልት ቦታ ውስጥ ወይም በምታልፍበት ቤት ደጃፍ ላይ ከምታያት እናት ጋርም ትነጋገር ዘንድ ትቆም ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜም ለምግብ ወይም ለልብስ ፍላጎት ያላት መሆንዋን ታገኝ ነበር፤ ወደ ቤትም ሔዳ ከቤቷ ከራስዋ አንዳች ነገር ታመጣላት ነበር፡፡ ከሞተች በኋላ ብዙ ዓመታት ቆይተው እርሷ ከምትኖርበት ሸለቆ ያሉት ጐረቤቶች ትንሿን ሸበቶ ሴት ስለ የሱስ በፍቅር ሁልጊዜ ስትነግራቸው የነበረችውን ትዝ ይላቸው ነበር፡፡ CCh 19.7
በሞተች ጊዜ ከሚያስፈልጋት ፍላጎትና ለሕይወቷም መደገፊያ ከሆነው በላይ ትንሽ ነበራት፡፡ እርሷ ምሳሌ አድርገው ይመለከቷት ዘንድ ሌሎችን አልጠየቀችም፤ እሷ ከኛ አንድዋ የነበረች ፤ ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት የሆነች በተነሣው ጌታዋ ትሩፋቶች የምታምን፤ በታማኝነት ጌታ አደራ የሰጣትን ሥራ ትሠራ ዘንድ የተጣጣረች ናት፡፡ እንዲሁም በልቧ እምነት አድርጋ እስከ ሕይወቷ መጨረሻ በክርስቲያናዊ ሁናቴዋ የጸናች ናት፡፡ CCh 20.1